ተፈጥሮ
የያዩ የቡና ደን ባዮሰፌር ሪዘርቭ/ ጥበቃ በልዩ የተፈጥሮ እሴቱ እንደምከተለዉ ልገለጽ ዪችላል፡
የገጠር ኑሮ ኢኮኖሚያዊ ችግር
የብዝሃ ህይወት ሀብት የበለፀገ ቢሆንም በአካባቢው ያለው የገጠር ህዝብ ኢኮኖሚያዊ ተግዳሮቶች የተደቀኑበት ሲሆን ህይወቱ በዋናነት በአነስተኛ ግብርና ላይ የተመሰረተ የአትክልት ፣ የእህል እና የቡና ልማትን ያካትታል ።የእንስሳት እርባታ ለገቢያቸው አስተዋጽኦ ያደርጋል፡፡ የኃይል አቅርቦቱ በዋናነት በእንጨትና በከሰል ላይ የተመሰረተ ነው፤ ብዙውን ጊዜ በህገ-ወጥ መንገድ ከደን ሃብቶች የምቆረጥ ነዉ፡፡
የባህል ቅርስ እና ባህላዊ ሀብት አስተዳደር
ተፈጥሮ በአውድ ውስጥ
በኦሮሞ ባህል ውስጥ ተፈጥሮ የተከበረ ቦታ አለው፤ ደኖች፣ ወንዞች፣ ዛፎች እና ህይወት ያላቸው ፍጥረታት በጣም የተከበሩ ናቸው፡፡ በኦሮሞ ማህበረሰብ እምብርት ላይ ያለው የገዳ ስርአት ማህበረሰባዊ እምነትና ተግባር የተቀደሱ ቦታዎችን እና አጋጣሚዎችን የሚሰይም ስርዓት ነው ። የጋዳ ስርዓት ባህላዊ የአስተዳደር ደንቦችን ይወስናል ፣ዛፎችን ከመቁረጥ ወይም ጅረቶችን መቀየር የተከለከለ ነው ። እነዚህን ደንቦች መጣስ ከባድ መዘዞች ያስከትላል፡፡ ከሚታወቁት እጅግ ሁሉን አቀፍ የአገሬው ተወላጅ አስተዳደር ስርዓቶች አንዱ እንደ መሆኑ መጠን ገዳ በዩኔስኮ እንደ አውሮፓውያን አቆጣጠር በ 2016 የማይዳሰስ የዓለም ባህላዊ ቅርስ ሆኖ እውቅና አግኝቷል ።
የአገር ውስጥ ተቋማት አስፈላጊነት
በአካባቢው አውድ ውስጥ፣ ኦዳ (Ficus) የዛፍ ዝርያ ፣ በማህበረሰብ ጉዳዮች ላይ ለመወያየት ፣ ለሰላም ፣ለዝናብ እና ለብልጽግና ፀሎት ለሚያደርጉ የሀገር ሽማግሌዎች ስብሰባ እንደ ጥላ ሆኖ ያገለግላል ። እንደ ጥቁር እንጨት፣ ግራር፣ ዝግባ እና ሾላያሉ ሌሎች ዛፎችም በተወሰኑ ስነ-ስርዓቶች ላይ ሚና ይጫወታሉ።ደኑ ለኦሮሞ ህዝብ ኑሮ ያለው ፋይዳ ከፍተኛ ሲሆን የባህል ሃብት አስተዳደር ተቋማት መኖራቸው የደን ሽፋኑን በጊዜ ሂደት አነስተኛ ለውጥ በማምጣት እንዲጠበቅ ትልቅ አስተዋፅኦ አበርክቷል ። ባህላዊ ደንቦች ፣ በግዛት ላይ የተመሰረቱ መደበኛ ያልሆኑ አስተዳደራዊ መዋቅሮች (tuulla፣ xuxee እና shane) እና የሽማግሌ ምክር ቤቶች (ሙቾ፣ሰሊጊ እና ጃርሳቢያ)፣የደን ጥበቃ እና ዘላቂ የሀብት አጠቃቀም ጠባቂዎች ናቸው ።
»የገዳ አስርዓት በአካባቢ ባህል ፣ በማህበራዊ መዋቅር እና በዘላቂ የተፈጥሮ ሀብት አያያዝ መካከል ያለውን ወሳኝ ግንኙነት ይወክላል ።«
ሳይንስ እና ጥበቃ
አብዛኛው የባዮስፌር ሪዘርቭ ጥብቅ(ዋና) ዞን እና የወንዞች አካባቢ ስነ-ምህዳሮች በአንፃራዊነት ገና ያልተመረመሩ ስሆን ፣እስካሁን ድረስ የተካሄዱት የተወሰኑ ጥናቶች በጥቂት ዝርያዎች ወይም ስነ-ምህዳራዊ ግንኙነቶች ላይ ነዉ ።አሁን ያለው ጥናት በዋናነት በእጽዋት ህይወት ላይ ያተኮረ ሲሆን በተለይም በኮፊ አረቢካ ዚርያ እና ሌሎች ጠቃሚ እፅዋት (የተባዙ እና ያልተባዙ) ዘረ መል ላይ ትኩረት አድርጓል ።የአከባቢውን ባዮሎጂካል ብዝሃነት አጠቃላይ ግምገማ እና ክትትልን ጨምሮ ተጨማሪ ምርምር ያስፈልጋል ።