ያዩ ቡና ደን ባዮስፌር ሪዘርቭ

የብዝሃ ሕይወት  ቦታ በአደጋ ላይ

በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ የሚገኙት የሞንታኔ የዝናብ ደኖች የምስራቅ አፍሮሞንታን የብዝሃ ህይወት ቦታ አካል ናቸው።የቀሩት ጥቂት የደመና ደን አካባቢዎች ለኢትዮጵያ ብቻ ሳይሆን ለዓለም አቀፍ ጠቀሜታ ያላቸው ናቸው። ከአስደናቂ የዕፅዋትና የእንስሳት ዝርያዎች ልዩነት በተጨማሪ እነዚህ ደኖች በዓለም ላይ ብቸኛውን የጫካ አረብቢያ ቡና (Coffee Arabica) የያዙ ናቸው።

ምንም እንኳን ሥነ-ምህዳራዊ እና ባህላዊ ጠቀሜታ ቢኖረውም ፣ የከፍታማ ቦታ ደን ሥነ ምህዳሩ በፈጣን የደን ምንጣሮና መራቆት ተግዳሮቶቸ ዉስጥ ሥሆን ፣ይህም በዋነኝነት በማህበራዊ፣ኢኮኖሚያዊ እና ፖለቲካዊ ጉዳዮች ባለፉት ጥቂት አስርት ዓመታት ውስጥ ነው። ዛሬ፣ከእነዚህ ከፍታማ  የደን ቦታዎች (አፍሮሞንታን) ጥቂቶቹ በዩኔስኮ ሰው እና ባዮስፌር (MaB) ፕሮግራም ስር ተሰይመዋል።

Footer Top

የባዮስፌር ሪዘርቭ ለመሆን የሚደረገው ጉዞ

የያዮ አካባቢን እንደ ባዮስፌር ሪዘርቭ የመመደብ ሃሳብ መነሻው በ2005 አካባቢው በፈጣን የደን ምንጣሮና መመናመን ዉስጥ መሆኑን ባስተዋሉ በርካታ ባለድርሻ አካላት ስጋት ላይ የተመሰረተ ነው ።የአካባቢና  የቡና ደን ፎረም (ECFF) የመሪነት ድርሻዉን በመዉሰድ የማመልከቻ ሂደቱ ተጀምሮ ፣ በ2010 ‹Yayu Coffee Forest Biosphere Reserve› የመጨረሻ ስያሜዉን አገኝቷል ።

ያዩ የሚለው ስም መጠቀሙ ሁል ጊዜ በአካባቢው ማህበረሰቦች ሲተች ቆይቷል።የባዮስፌር ሪዘርቭ  በዕጩነት ለዩኔስኮ ዕውቅና ሲቀርብ፤ በደርግ ዘመን ትኩረት የተሰጠው የደን ቦታ ተብሎ በፌዴራል ደረጃ በይፋ እውቅና ያገኘው “ያዩ” በሚል ስያሜ ነበር ። አሁንም“ያዮ” የሚለው ስም በክልሉ ውስጥ እንደ ኦሮሞ ጎሳ ስም ትልቅ ቦታ ስላለው በማህበረሰቡ ዘንድ ተቀባይነት አለው ። ለማጠቃለል ያህል፣ “ያዮ” የሚለው ስም ከሰዎች ማንነት ጋር መቆራኘቱ እና መጣጣሙ ይፋዊውን ስያሜ ቀጣይነት ያለው ተቃውሞ ያስከትላል ።

የያዩ ቡና ደን ባዮስፌር ሪዘርቭ ሶስት ቁልፍ ተግባራትን ያከናዉናል

ጥበቃ

አካባቢው በአረቢካ ቡና (Coffea Arabica) ውስጥ የዘረ መል ልዩነትን በመጠበቅ ረገድ በክልላዊ እና አለም አቀፋዊ ጠቀሜታ የታወቀ ሲሆን የዚህ ዝርያ ትልቁ፤ ሰፊ እና የተለያየ ሲነህዪወት መኖሪያ ነው ። በባዮስፌር ሪዘርቭ ዉስጥ ከ450 በላይ እፅዋት፣ 50 አጥቢ እንስሳት፣ 30 ወፎች እና 20 ተሳቢ ዝርያዎች የምኖሩ ስሆን፤ በአጠቃላይ ከ100 የሚበልጡ የዕፅዋት ፣ የአእዋፍ እና አጥቢ እንስሳት ዝርያዎች አሉ ። በ IUCN ቀይ ዝርዝር ላይ በመመስረት ቢያንስ 44 የተመዘገቡ የባዮስፌር ሪዘርቭ ዝርያዎች በአለም አቀፍ ደረጃ የመጥፋት አደጋ ተጋርጦባቸዋል።

ቀጣይነት ያለው ልማት

ባዮስፌር ሪዘርቭ ዘላቂ ኢኮኖሚያዊና ሰብአዊ ልማትን ያጎለብታል፣ይህም ልማት በማህበራዊ እና በስነ ምህዳር ዘላቂነት ያለው መሆኑን ያረጋግጣል ። የያዮ አካባቢ በኢትዮጵያ የቡና ኢንዱስትሪ ውስጥ ወሳኝ ሚና ያለው ሲሆን የአብዛኛው ህዝብ ዋና ገቢም ከቡና ነው ። አርሶ አደሮች በቅመማ ቅመምና የማር ምርት በመሰማራት ለአካባቢው ኢኮኖሚ አስተዋፅዖ ያደርጋሉ ።

ምርምር እና ትምህርት

የባዮስፌር ሪዘርቭ ዋና ዋና ተግባራት የጥናት ሙከራ ስራዎችን መደገፍ ፣ ዘላቂ ልማትን ማጎልበት፣የአካባቢ ትምህርትን ፣ ስልጠናን ፣ ምርምርን እና ጥበቃን በአካባቢ ፣ በክልላዊ ፣ በአገር አቀፍ እና በአለምአቀፍ ደረጃ ከጥበቃ እና ዘላቂ ልማት ጋር የተያያዙ ስራዎችን መደገፍ ነው።አካባቢው ለዘላቂ ልማት፣ለቡና፣ለጤና እና ለሲቪል ማህበረሰብ ተሳትፎ የእሴት ሰንሰለት ማሻሻል ላይ ያተኮሩ በርካታ የምርምር ስራዎችን እና ፕሮጀክቶችን ያስተናግዳል።

ባጠቃላዪ የያዩ ቡና ደን ባዮስፌር ሪዘርቭ የህዝቡን ማህበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነት እየደገፈ ያለውን ልዩ የብዝሀ ህይወት እና የበለፀገ የቡና ቅርስ ለመጠበቅ ጥበቃን፣ዘላቂ ልማትን እና የምርምር ውጥኖችን አጣምሮ የያዘ ዘርፈ-ብዙ ስነ-ምህዳርን ይወክላል ።

BG