አግባብነት ያላቸው ተዋናዮች

የኦሮሚያ አካባቢ ጥበቃ ባለ ስልጣን የማኔጅመንት እቅዱን ለማስፈጸም መደበኛ ሀላፊነቱን ቢወስድም በአካባቢው የሚገኙ የተለያዩ መንግሥታዊና መንግሥታዊ ያልሆኑ አካላት ዕቅዱን በመደገፍ አዳዲስ ፕሮጀክቶችን እና ውጥኖችን በማነሳሳት በንቃት በመሳተፍ ላይ ናቸው ። በፌዴራል ደረጃ እንደ የኢትዮጵያ ደን ልማት ፣ የኢትዮጵያ ብዝሃ ሕይወት ኢንስቲትዩት፣የኢትዮጵያ ቡናና ሻይ ባለስልጣን ያሉ ቁልፍ የፈደራል አካላት በተፈጥሮ ሀብት አያያዝ ላይ ከፍተኛ ሚና ይጫወታሉ።

Footer Top

በክልል ደረጃ የኦሮሚያ ደንና ዱር እንስሳት ኢንተርፕራይዝ የደን እና የዱር እንስሳት ሀብትን አያያዝ የመቆጣጠር ግዴታ አለበት፤ የኦሮሚያ ግብርና ቢሮ ደግሞ ዘላቂ የግብርና አሰራርና ፖሊሲዎችን የማስተዋወቅ ኃላፊነት አለበት ። የኦሮሚያ ኅብረት ስራ ማስፋፊያ ኤጀንሲ የህብረት ስራ ማህበራት ለኢኮኖሚ እድገት ኢንድሰሩ ያግዝዛል።

በአከባቢ ደረጃ መንግስታዊ ያልሆኑ አካላት የህብረት ስራ ማህበራት ፣ የሴቶች አደረጃጀቶች እና መደበኛ ያልሆኑ ተቋማት እንዲሁም ቁርጠኛ የልማት ወኪሎች እና የቀበሌ አስተዳዳሪዎች ቀጥተኛ እና ሊለካ የማይችል ተፅእኖ አላቸው።እንደ ሶርገባ የገበሬዎች ህብረት ስራ ዩኒየን ያሉ ማህበረሰብ አቀፍ ድርጅቶች ፣ እንደ መቱ ዩኒቨርሲቲ ያሉ የምርምር ድርጅቶች እና የተለያዩ ንቁ መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች እንደ ECFFEWNRANABU Ethiopia እና ሌሎችም ለአካባቢው ዘላቂ ልማት የበኩላቸውን አስተዋጽኦ አድርገዋል።

BG