BG
0

ፏፏቴዎች

0

ወንዞች

0

ዋሻዎች

BG

የያዩ ደን ቡና ባዮስፌር ሪዘርቭ ኢትዮጵያ ውስጥ ከሚገኙት ያልተመናመኑ የአፍሮሞንታኔ የዝናብ ደን አካባቢዎች አንዱ ሲሆን የጫካ አረብካ ቡና ለብዙ ማህበረሰቦች መኖሪያ እና ገቢ ማስገኛም ነው። የአከባቢው ዘርፈ ብዙ ኢኮኖሚያዊ እና ተፈጥሯዊ እሴቶች ለጫካ አራቢካ ቡና፣ ለዩኔስኮ ባዮስፌር ሪዘርቭ እና በርካታ የአለም አቀፍ ጠቀሜታ ያላቸው ጠቃሚ ወፎች እና እንስሳት(IBA) ቦታዎች እንደ ብሄራዊ የዘረመል መጠበቂያ ስያሜው እውቅና አግኝተዋል። በጣም አስፈላጊው ነገር፣ የአከባቢው ስም በትክክል “ያዮ” ነው፣ ግን በ UNESCO ስር እንደ “Yayu” ተመዝግቧል

Yayu Montane Rainforests and Coffee Culture

የሞንታኔ የዝናብ ደኖች እና የቡና ባህልዝምድና

የያዩ ደን ቡና ባዮስፌር ሪዘርቭ መልክአ ምድር በ ከፍታማ (ተራራማ) የዝናብ ደኖች፣ ረግረጋማ ቦታዎች፣ የግጦሽ መሬት እና አነስተኛ የእርሻ ቦታዎች፣ ዋሻዎች እና ፏፏቴዎች፣  አስደናቂ ትዕይንቶችን ያያዘ ነው። ለባዮስፌር ሪዘርቭ መጠሪያ አስተዋጽኦ በማድረግ ቡና ለኢትዮጵያ ከዚህ በፊት ታይቶ የማይታወቅ ኢኮኖሚያዊ ጠቀሜታ ያስገኘ ከመሆኑም በላይበኢትዮጵያ ባህል ውስጥ ከፊተኛ ሚና ይጫወታል። በአካባቢው ቡና በተለያዩ መንገዶች ይመረታል፡ እንደ ጓሮ ተክል-ቡና በቤተሰብ ጓሮዎች ውስጥ፣ አን ሰፋፊ እርሻዎች ነገርግን በዋነኝነት እንደ የደን ቡና በዋናው የደን ሽፋን ስር በሰፊዉ ይገኛል።

የኢትዮጵያን የተፈጥሮ እና የባህል ሀብቶች መጠበቅ

በዋናው የጥብቅ ደን ክልል ዉስጥ ተፈጥሯዊ እፅዋቶች ተጠብቀው የምገኙ ስሆን፣ይህም ለተፋሰስ ጥበቃ ትልቅ ሚና ይጫወታሉ፡ እንደ ጌባ፣ ዶጊ፣ ሳኪ እና ሰሴ ያሉ ትናንሽ ወንዞች የናይል ወንዝ ዋና ገባር በሆነው ባሮ ወንዝ ውስጥ ይገባሉ። የያዩ ደን ቡና ባዮስፌር ሪዘርቭ እነዚህን የመጨረሻ ቅሪቶች የአፍሮሞንታን ደመና ደኖችን ለመጠበቅ የሚጫወተው ሚና የማዪናቅእና ከፍተኛስሆንአለም አቀፍ ጠቀሜታም አለው። የምስራቅ አፍሮሞንታን የብዝሃ ህይወት ቦታ አካል የሆነው የያዩ ቡና ደን ባዮስፌር ሪዘርቭ ለኮፊ አረቢካ ጫካብዛህዎት ጠቃሚ የጂን ክምችት ብቻ ሳይሆን የመጥፋት አደጋ ተጋርጦባቸዋል ተብለው የሚታሰቡ ሌሎች የእፅዋት እና የእንስሳት ዝርያዎች መገኛ ከመሆኑም በላይእንደዚህ አይነት የደመና ደኖች ሌላ ቦታ የለም፡፡ እንደዚህ አይነት  አካባቢዎች ሁሉን አቀፍ ባህላዊና ታሪካዊ ጠቀሜታቸው በብዙ የአርኪዮሎጂና የ ሥርዓት ሥፍራዎች በመባል ይገለጻሉ፡፡

የያዩ ቡና ደን ባዮስፌር ሪዘርቭ ብዙ እሴቶችን የያዘ፣ የአካባቢ ጥበቃ ከባህላዊ ቅርስ ጋር የተዋሃደበት ልዩ ቦታ ነው። ተግዳሮቶች ቢያጋጥመውም ለተፈጥሮ ክብር ባለው  የዳበረ ባህል በመመራቱ ዘላቂ የሆነ የተፈጥሮ እና የኑሮ ዘይቤን አጣምሮ የማኖር አቅም አለው።

BG